አውሮፕላኑ የወደቀው በምሥራቅ ሸዋ ዞን ጊምቢቹ ወረዳ ነው

90

አዳማ  መጋቢት 1/2011 የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች አውሮፕላን በረራ ላይ እያለ ዛሬ ማለዳ የተከሰከሰው በምሥራቅ ሸዋ ዞን ጊምቢቹ ወረዳ  መሆኑን ነው ፖሊስ ያስታወቀው።

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት  እንደገለጹት አደጋው የተፈጠረው ሂጄሪ በሚባል ስፍራ ነው።

ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ሲበር የነበረው አውሮፕላኑ  በፊትለፊት  በወደቀበት ሥፍራ 10 ሜትር ያህል ጉድጓድ መፍጠሩንም ተናግረዋል።

አደጋው በተከሰተበት ሥፍራ የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት መገኘታቸውንም አስታውቀዋል።

በአውሮፕላኑ 149 መንገደኞችና ስምንት የአየር መንገዱ ሠራተኞች እንደነበሩበት ተገልጿል።

አውሮፕላኑ አደጋው የደረሰበት ከቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት በተነሳ በስድስት ደቂቃ ልዩነት ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ44 ደቂቃ ላይ እንደ ነበር የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም