በነቀምቴ ከ3 ሺህ 500 በላይ ወጣቶች ሥራ እድል ተፈጥሯል

59

ነቀምቴ የካቲት 25/2011 በነቀምቴ ከተማ ድህነትና ሥራ አጥነትን ለመቀነስ እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ ከ3 ሺህ 500 በላይ ወጣቶች በሥራ ፈጠራ ተጠቃሚ ሆኑ።

የከተማው የሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ጽህፈት ቤት  ምክትል ኃላፊ አቶ ታሪኩ ብርሃኑ እንዳሉት ወጣቶቹ ተጠቃሚ የሆኑት በግማሽ ዓመቱ በተከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ነው።

ወጣቶቹ ሥራዎቹን ያከናወኑት በንግድ፣በኮንስትራክሽን፣በአገልግሎት፣በከተማ ግብርናና በማምረቻ ዘርፎች ተደራጅተው በመንቀሳቀስ  ነው።

ከተጠቃሚዎቹ 652 የሚሆኑት የከፍተኛ ትምህርትና የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ምሩቃን መሆናቸውንም አስረድተዋል።

ወጣቶቹ በእንቅስቃሴያቸው ውጤታማ እንዲሆኑ 27 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር እንደተመቻቸላቸውም ገልጸዋል።

በተጨማሪ 32 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ የገበያ ትስስር እንደተፈጠረላቸው ኃላፊው ተናግረዋል።

ዘንድሮ ሥራ ውስጥ የገቡ ወጣቶች ቁጥር ከዓምናው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በ13 በመቶ ዕድገት እንዳስመዘገበ አቶ ታሪኩ አስረድተዋል።

ታዬ ማሙዬና ደመላሽ ገለታ የተባሉ ወጣቶች በተሰማራንባቸው የሥራ ዘርፎች በጥራት ሰርተው ዕውቅና ለማግኘት እንሰራለን ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ብር ወጪ የተረከቡትን ፕሮጀክት በተያዘለት ጊዜ አጠናቀው ለማስረከብ በመሥራት ላይ እንደሚገኙም  አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም