የሱዳኑ ፕሬዚዳንት አልበሺር ከገዥው ፓርቲ ሊቀመንበርነታቸው ተነሱ

79

የካቲት 22/2011 የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሺር ከገዥው ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበርነታቸው መውረዳቸው ተገልጿል።
በምትካቸውም የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር አህመድ ሞሃመድ ሃሩን ፓርቲው አጠቃላይ ጉባኤ እስከሚያካሂድ የአልበሺርን ቦታ መረከባቸው ነው የተነገረው።
ሀሩን በዚህ ሳምንት የሱዳን ገዥ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።
በሱዳን ከታህሳስ ወር 2018 ጀምሮ እስከዛሬ ያልተቋረጠው የዜጎች ተቃውሞ አልበሺር ከፓርቲ ሃላፊነታቸው እንዲለቁ ማስገደዱን ተንታኞች እየገለጹ ቢሆንም ፕሬዚዳንቱ ከዚህ ቀደምበተቃውሞ ፍራቻ ሳይሆን በምርጫ ብቻ ስልጣናቸውን እንደሚለቁ መናገራቸው ይታወሳል።
ሱዳን በ2020 ምርጫ እንደሚታካሂድ ይጠበቃል።
አልበሺር ባሳለፍነው ሳምንት ለአንድ ዓመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያወጡ ሲሆን እሰተዳደራዊ መዋቅሩን በመበተን አዳዲስ ፖለቲካዊ እና ወታደራዊ ሹመት ሰጥተዋል።
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ክልከላ ቢደረግም ተቃውሞው እስከዛሬ ድረስ መቀጠሉን መረጃዎች ያሳያሉ።
ምንጭ፦ሲጂቲኤን

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም