ፖሊስ በአዲስ አበባ የተጠራ ሰላማዊ ሰለፍ የለም አለ

70

አዲስ አበባ የካቲት 16/2011 የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ነገ በአዲስ አበባ ከተማ የተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ አለመኖሩን አስታወቀ።

"በመስቀል አደባባይ ነገ ሰላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል" በሚል በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተላለፈው ዘገባ ሀሰተኛ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነገ ምንም ዓይነት የሠላማዊ ሰልፍም ሆነ ስብሰባ እናድርግ የሚል ጥያቄ ያልቀረበለት መሆኑን ለኮሚሽኑ የገለጸ መሆኑን ጠቅሷል።

ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው በመሆኑ "ሰልፍ እንወጣለን" በሚል በህብረተሰቡ ላይ የጸጥታ ችግር ለመፍጠር የሚፈልጉ አካላት ከተግባራቸው እንዲታቀቡም ኮሚሽኑ አሳስቧል።

የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል ይህን ተላልፈው በሚገኙ አካላት ላይ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም