ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንትን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

60

የካቲት 14/2011- ሁለቱ ወገኖች በሀገራቱ መካከል ያለውን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ ስለማጠናከር፣ በሶማሊላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ደኅንነት ስለማስጠበቅና በሰላምና ደኅንነት ዙሪያ ተባብሮ ስለመሥራት ተወያይተው ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል፡፡

የሶማሊላንድ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲን በበኩላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ለቀጣናው ውህደት የወሰዷቸውን እርምጃዎች በማንሣት አስተዳደራቸው ከሶማሊያ መንግሥት ጋር በይበልጥ ተቀራርቦ እንዲሰራ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ያቀረቡትን ጥሪ እንደሚቀበሉ ገልፀዋል።

በተጨማሪም ወደፊት በጋራና በተናጠል ቀጣይ ውይይቶችን ለማካሄድ የተስማሙ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች ስለ ወደብ አጠቃቀምና ሌሎችም የኢኮኖሚ ትሥሥሮችም ላይ ተነጋግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም