በከተሞች ፎረም የቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎችና የፓናል ውይይቶች ውጤታማ ነበሩ

72

አዲስ አበባ የካቲት 13/2011 በከተሞች ፎረም የቀረቡ ጥናታዊ ጽሁፎችና የፓናል ውይይቶች ውጤታማ እንደነበሩ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ገለጸ።

ሚኒስትሩ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት ፎረሙን በማስመልከት የቀረቡት 23 ጥናታዊ ጹሁፎችና የፓናል ውይይቶች ስኬታማ ነበሩ።

ፓናሎቹ ግብዓት ለማሰባሰብ ፣ ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን ለማሻሻል፣ በከተማ ልማት እቅዶች ላይ በትኩረት መስራት የሚያስፈልጋቸውን ርዕሰ ጉዳዮች ለመለየት ጠቃሚ ግብዓት የተገኘባቸው ነበሩ ብለዋል።

ሶስተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለማቀድ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች የተንሸራሸሩባቸው እንደነበሩም አክለዋል።

በፓናሎቹ ምሁራን፣ የጅግጅጋ ነዋሪዎች፣ የፎረሙ ተሳታፊዎችና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን ይህም ለከተሞች እድገት ትኩረት ሰጥተው ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት ያሳየ መሆኑን ሚስትሩ ተናግረዋል።

ከየካቲት 8-14 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የቀረቡትና የተካሄዱት ጥናታዊ ጽሁፎችና የፓናል ውይይቶች ዛሬ ተጠናቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም