የደኢህዴን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው

81

ሃዋሳ የካቲት 12/2011 የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ / ደኢህዴን/  ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በአርባምንጭ ከተማ  መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡

ከደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በስብሰባው በ10ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎች የስድስት ወራት አፈጻጸም ይገመግማል፡፡

የፖለቲካና የድርጅት ጉዳዮች ፣ ሃገራዊና ክልላዊ የፖለቲካና ጸጥታ ጉዳዮች ላይም  ይወያያል፡፡

በእድገትና ትራንስፎሜሽን እቅዱ መሰረት በከተማና  ገጠር አካባቢዎች የተከናወኑ ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም ላይም ይመክራል፡፡ 

ስራ አስፈጻሚው በስብሰባው እነዚህን ጉዳዮች እስከ መጪው አርብ ከገመገመ በኋላ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ደግሞ በተመሳሳይ አጀንዳ እንደሚመክር የጽህፈት ቤቱ  መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም