በጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፅህፈት 339 ህገ-ወጥ የሞባይል ቀፎ መያዙን አስታወቀ

102

ደሴ የካቲት 6/2011 በህገ-ወጥ መንገድ ከቆቦ ወደ ወልዲያ ሲጓጓዝ የነበረ 339 የሞባይል ቀፎ መያዙን የኢፌዴሪ ጉምሩክ ኮሚሽን የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሰማን ዳዉድ ለኢትጵያ ዜና አገልግሎት እንዳስታወቁት የሞባይል ቀፎው የተያዘው በ5/2011 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ በወልዲያ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ነው።

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-75474 አዲስ አበባ በሆነ ኤፍ ኤስ አር የጭነት መኪና ወደ ወልድያ ሊገባ ሲል በመቆጣጠሪያ ጣቢያው በተደረገ ፍተሻ ሊያዝ መቻሉንም አስረድተዋል።

ሞባይሉ ከየት እንደመጣና የቀፎውን ስሪት የማጣራት ስራ እየተከናወነ ነው ያሉት ሃላፊው 375 ሺህ 600 ብር ግምት እንዳለውም አብራርተዋል።

ንብረቱን ሲያጓጉዙ የተገኙት አሽከርካሪውን ጨምሮ ረዳቱና ተጠርጣሪው የንብረቱ ባለቤት በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም