ኢትዮጵያ የአፍሪካ አገሮች ቡድን ሊቀ-መንበርነት ቦታ ያዘች

82
አዲስ አበባ ሚያዝያ 26/2010 ኢትዮጵያ በመንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ አገሮች ቡድን ሊቀ-መንበርነትን ቦታ ለአንድ ወር ያዘች። ከዚህ ቀደም ቦታውን ይዛ ከቆየችው ከማሊ ቦታውን ተረክባለችል። በድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ዶክተር ተቀዳ ዓለሙ ከማሊ አቻቸው ኢሳ ኮንፎሮ ሊቀ-መንበርነቱን ተረክበዋል። የአፍሪካ ቡድኑ በመንግሥታቱ ድርጅት ውስጥ ከተደራጁ አምስት ቡድኖች መካከል አንዱ ነው። አገሮች በጂኦ ፖለቲካዊ አቀማመጣቸው እንዲቧደኑ በማድረግ በድርጅቱ ውስጥ ያሉትን ሹመቶች አማካኝነት አካባቢያዊ ተዋጽዖውን ይቆጠጣሩበታል። በዚህና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አካባቢያዊ ወይንም ቀጣናዊ ምክክር ለማድረግ አገራት ቡድኑን እንደሚጠቀሙበት መረጃዎች ያሳያሉ። የአፍሪካ ቡድን 53 አባል አገሮችን ይዟል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም