ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አሕመድ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

57

አዲስ አበባ 2/2011 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አሕመድ  ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል የሁለትዮሽ ትብብር እኤአ ከ1995 ጀምሮ የተመሰረተ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያን በአፍሪካ የኖርዌይ ትልቋ አለምአቀፍ ትብብር እንድትሆን እንዳስቻላትም ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንኑ ትብብር በማድነቅ የስካንዲኔቪያ አገራትን ተሞክሮ አገራቱ በጋራ እንዲያድጉ እድል እንደከፈተላቸው አውስተዋል።

ይህም ለአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ውህደት እንደ ተምሳሌት የሚወሰድ ነው ሲሉ መናገራቸውም ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ጠቁሟል። 

የኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥና የአካባቢው ውህደት ጅማሮዎችን በማድነቅ አገራቸው የምታደርገውን እርዳታ በተለይም በትምህርት ዘርፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም