አዲስ አበባ ፖሊስ በብሔራዊ የክለቦች የቦክስ ውድድር ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አግኘ

61

አዲስ አበባ ጥር 30/2011 አዲስ አበባ ፖሊስ በወላይታ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ሁለተኛው የብሔራዊ የክለቦች

የቦክስ ውድድር ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል።

ትናንት በተጀመረው ውድድር በሁለቱም ጾታዎች ከ9 ክለቦች የተውጣጡ 80 ተወዳዳሪዎች እየተሳተፉ ነው።

በወንዶች ከ49 እስከ 91 ኪሎ ግራም በሴቶች ደግሞ ከ48 እስከ 60 ኪሎ ግራም ውድድሮቹ የሚካሄድባቸው የክብደት ዘርፎች ናቸው።

የድሬዳዋ ከተማ ፣ ማራቶን፣ ወላይታ ጦና፣ አዲስ አበባ ፖሊስ፣ ፌደራል ፖሊስና ፌደራል ማረሚያ ቤቶች በውድድሩ ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙት ክለቦች መካከል ይጠቀሳሉ።

የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን የውድድርና ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ስንታየሁ ተስፋዬ ለኢዜአ እንደገለጹት ትናንትውድድሩ ሲጀመር ሶስት የፍጻሜ ጨዋታዎች ተካሄደዋል።

በዚሁ መሰረት በ51 ኪሎ ግራም ሴት የአዲስ አበባ ፖሊሷ ሮማን አሰፋ የወላይታ ጦናዋን ጥሩነሽ ኢሳያስን፤ በ60 ኪሎ

ግራም ሴት ቤተል ወልዱ ከአዲስ አበባ ፖሊስ የወላይታ ጦናዋን በሀይሏ ካሴን በተመሳሳይ በነጥብ ማሸነፋቸውንተናግረዋል።

ይህንን ተከትሎም አዲስ አበባ ፖሊስ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘቱን ጠቅሰዋል።

በ91 ኪሎ ግራም ወንድ የፌደራል ፖሊሱ ሙሉቀን መልኬ የአዲስ አበባ ፖሊሱን ታምራት አበበ በበቃኝ አሸንፏል።

ከሶስቱ የፍጻሜ ውድድሮች በተጨማሪ ትናንት በወንድ 60፣ 64 እና 75 ኪሎ ግራም በሴት በ54 ኪሎ ግራምየማጣሪያ ጨዋታዎች ተካሄደዋል።

ዛሬም ውድድሩ ሲቀጥል በወንዶች 49፣ 52፣ 56፣ 60፣ 69 እና 81 ኪሎ ግራም እንዲሁም በ48 ኪሎ ግራምየማጣሪያ ውድድሮች እንደሚካሄዱ ነው አቶ ስንታየሁ ያስረዱት።

የውድድሩ ዓላማ በስፖርቱ ብቁና ውጤታማ ተወዳዳሪዎችን መመልመልና የውድድር አማራጭ መፍጠር እንደሆነ ተገልጿል።

በሞሮኮ አዘጋጅነት በነሐሴ ወር 2011 ዓ.ም በሚካሄደው 12ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች በቦክስ ስፖርትኢትዮጵያን የሚወክሉ ስፖርተኞችን ለመምረጥም ውድድሩ እንደሚረዳም ተናግረዋል።

ብሔራዊ የክለቦች ቦክስ ውድድር በዓመት አራት ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን የመጀመሪያው ውድድር ህዳር 2011 ዓ.ም

በድሬዳዋ ከተማ እንደተካሄደ ይታወሳል። ቀጣዮቹ ሁለት ውድድሮችም በጅግጅጋና አዲስ አበባ ይካሄዳሉ።

በቦክስ ውድድሮቹ የተገኘው አጠቃላይ ውጤት ተደምሮ በሁለቱም ጾታዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ክለቦች የ2011

ዓ.ም የብሔራዊ የቦክስ ክለቦች አጠቃላይ አሸናፊ እንደሚሆንም አስረድተዋል።

ሁለተኛው የብሔራዊ የክለቦች የቦክስ ውድድር እስከ የካቲት 2 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።

በህዳር 2011 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ በተካሄደው የዓመቱ የመጀመሪያ ብሔራዊ የክለቦች ውድድር የድሬዳዋ ከተማየቦክስ ክለብ በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም