ለብርብርሳ ከተማ መንገድ ማሰሪያ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተገኘ

59

መቱ ጥር 28/2011 በኢሉአባቦር ዞን ለብርብርሳ ከተማ መንገድ ማሰሪያ ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተገኘ።

የገቢ ማሰባሰቢያ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ወንድሙ ተካልኝ እንደገለጹት ገንዘቡ የተሰባሰበው ለከተማው 6 ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ መንገድ ማሰሪያ ነው።

ለሦስት ቀናት በተካሄደው በገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር ድጋፍ ካደረጉ መካከል የዞኑ አስተዳደርና የዞኑ ሥራና ከተማ ልማት ጽህፈት ቤት ይገኙበታል።

በዞኑ ሥር የሚገኙ ወረዳዎች፣ የመንግስት ሠራተኞችና ባለሀብቶችም በድጋፉ መሳተፋቸውን የገለጹት ሰብሳቢው፣ የወረዳው አመራሮችም  ከደሞዛቸው 85 ሺህ ብር ለመስጠት ቃል መግባታቸውን ተናግረዋል።

በደቡብ ክልል የሸካ ዞንና ማሻ ከተማ አስተዳደሮችም ከ430ሺህ ብር በላይ  ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡

"በድጋፍ ቃል ከተገባው ገንዘብ ውሰጥ እስካሁን ከ600ሺህ ብር በላይ ተሰብሰቧል" ብለዋል።

እንደ ሰብሳቢው ገለጻ ለግንባታው ከሚያስፈልገው ሰባት ሚሊዮን ብር ነው ።

ብርብርሳ የኖኖ ሰሌ ወረዳ ርዕሰ ከተማ ናት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም