ሦስተኛው መላው የድሬዳዋ ሴቶች ጨዋታ ተጀመረ

64

ድሬዳዋ ጥር 26/2011 በዘጠኝ የስፖርት ዓይነቶች የሚካሄደውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሴት ስፖርተኞች የሚወዳደሩበት 3ተኛው የድሬዳዋ አስተዳደር መላው የሴቶች ጨዋታ ዛሬ ተጀመረ።

ውድድሩ ድሬዳዋን በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚያስጠሩ ስፖርተኞችን ለማፍራት ያግዛል ተብሏል፡፡

በመክፈቻ ሥነስርአቱ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አና ዑመር ውድድሩ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጎልበት እያገዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በውድድሩ በገጠርና በከተማ እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ባልሆኑ ተቋማት የሚሰሩ ሠራተኞች ተሳታፊ መሆናቸውንና ምርጥና ተተኪ ስፖርተኖችን ለማፍራት እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

በተለይ በቅርቡ ለሚጀመረው የሴቶች የዲቪዚዮን ክለቦች የእግር ኳስ ጨዋታ ላይ የሚካተቱ ተሳታፊዎች እንደሚመለመሉበት ነው ኮሚሽነር አና የገለፁት፡፡

" በውድድሩ በየካቲት ወር መጨረሻ ጂግጂጋ ከተማ ላይ በሚኪያሄደው ሀገር አቀፍ 3ተኛው የመላው የሴቶች ጨዋታ ድሬዳዋን የሚወክሉ ውጤታማ ስፖርተኞች  ይመለመላሉ " ብለዋል፡፡

በውድድሩ ላይ ስትሳተፍ የመጀመሪዋ መሆኑን የገለጸችው ወጣት ስፖርተኛ ቤተልሔም ትዕግስቱ በበኩሏ "ያለኝን ብቃት በማውጣት ድሬዳዋን በሀገር ደረጃ ለማስጠራት አጋጣሚውን አግኝቻለሁ" ብላለች፡፡

ሌላዋ ስፖርተኛ ሊና ኢሊያስ በበኩሏ " ስፖርት ኮሚሽን ውድድሩን ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን ለስፖርተኞቹ የአልባሳትና የእውቀት ድጋፍ በማድረግ ለውጤት ማብቃት አለበት " ብላለች፡፡

ሦስተኛው መላው የድሬዳዋ የሴቶች ጨዋታ በአትሌትክስ፣ በእግር ኳስ፣ በቼስ፣ በጠረጴዛ ቴኒስ፣ በፓራሊፒክ፣ መስማት በተሳናቸው እና በባህል ስፖርተኞች ለአንድ ሣምንት ይኪያሄዳል፡፡

በመክፈቻው ሥነ-ሥርዓቱ ላይ በተካሄሄደው የመረብ ኳስ ውድድር ቀበሌ 02 ቀበሌ 04ን ሁለት ለአንድ ሲያሸንፍ በጠረጴዛ ቴኒስ ቀበሌ 06 ቴሌን 3 ለባዶ በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም