የትግራይ ክልል አራተኛው መላው የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር ተጀመረ

68

መቀሌ ጥር 26/2011 አራተኛው የትግራይ ክልል መላው የትምህርት ቤቶች ስፖርታዊ ውድድር ዛሬ በአዲግራት ከተማ ተጀመረ።

ከ20 በላይ የስፖርት አይነቶች በሚካሄደው በዚህ ውድድር ከክልሉ 52 ወረዳዎች የተውጣጡ ከ7 ሺህ በላይ ስፖርተኞች ተገኝተዋል።

ስፖርታዊ ውድድሩ ከጥር 26 እስከ የካቲት 10 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚቆይ የትግራይ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ጉዳዮች ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ገብረማሪያም ዘሚካኤል አስታውቀዋል።

ሦስተኛው የክልሉ መላው የትምህርት ቤቶች ውድድር በአክሱም ከተማ መካሄዱ የሚታወስ ነው። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም