የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች የ100 ቀናት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እየተካሄደ ነው

70

አዲስ አበባ ጥር 20/2011 የሚኒስቴር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት የ100 ቀናት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት እየተካሄደ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ በተገኙበት እየተካሄደ ባለው ግምገማ ላይ ተቋማቱ ባለፉት 100 ቀናት ለማከናወን ይዘዋቸው የነበሩትን እቅዶች ክንውን አስመልክቶ ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።

በዚሁ መሰረት የገንዘብ ሚኒስቴር፣ የሰላም ሚኒስቴር፣ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪፖርቶቻቸውን አቅርበዋል።

ሚኒስቴሮቹ የዕቅዶቻቸውን የአፈፃፀም ስኬት፣ በሂደት ላይ የሚገኙና ቀሪ ስራዎቻቸውን በሪፖርታቸው አካተዋል።

የቀረበውን የአፈፃፀም ሪፖርት መነሻ በማድረግም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይን ጨምሮ ሚኒስትሮችና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

የሌሎች መስሪያ ቤቶችም ግምገማና ውይይት ቀጥሎ በነገው እለት እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ካቢኔያቸውን በአዲስ መልክ ማዋቀራቸውን ተከትሎ ሚኒስትሮች የ100 ቀናት ዝርዝር የሥራ እቅድ እንዲያዘጋጁ ማድረጋቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም