23 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ያስመዘገቡ 94 ኢንቨስተሮች ወደ ትግበራ ተሸጋግረዋል… የኢንቨስትመንት ኮሚሽን

1827

ጥር 16/2011 በውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ 94 ኢንቨስተሮች 23 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በማስመዝገብ ባለፉት አምስት ወራት ወደ ትግበራ መሸጋገራቸውን የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ ፡፡

የኢንቨስትመንት አማራጭና ምቹ ሁኔታን በማስተዋወቅ ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ዘርፉ ከተሰማሩት 94 ቱ ባለፉት አምስት ወራት 23.6 ቢሊዮን ብር በማስመዝገብ   ወደ ትግበራመሸጋገራቸውን በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ መኮንን ሀይሉ  ገልጸዋል ፡፡

በዘርፉ የተሰማሩ 23ነጥብ6 ቢሊዮን ብር የሚያስመዘግቡ 115 ፕሮጀክቶችን ወደ ትግበራ ለማሸጋገር ቢታደቀድም 94 ተሸጋግረዋል፡፡

እንዲሁም 7.3 ቢሊዮን ብር ካፒታል ካስመዘግቡ 90 ፕሮጀክቶች 69ኙ ወደ ምርት  መግባታውን ገልጸዋል፡፡

ከውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ዘርፍ ባለፉት አምስት ወራት ለማግኘት ካቀደው 2 ሚሊዮን ዶላር1 ነጥብ 53  ቢሊዮን ዶላር መገኘቱንና ያለፈው አመትም 3ነጥብ75 ቢሊዮን ዶላር እንደነበረም ዳይሬክተሩ  ገልጸዋል ፡፡

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ጋር በመተባበር የኢንቨስትመንት አማራጭንና ምቹ ሁኔታን በአለም አቅፍ ሲምፖዚየም፣ የንግድ ፎረም  መተዋወቁና  የሀገሪቱ ሰላም በመሻሻሉ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ   መጨመሩን ተናግረዋል፡፡

የግብርና፣ማንፋክቸሪንግና የአገልግሎት ዘርፉ ዋነኛ የሀገሪቱ የኢንቨስትመንት አማራጮች ናቸው  የሚሉት አቶ መኮንን በአሁኑ ሰዓት የማንፋክቸሪግ ዘርፉ ካለው  ከፍተኛ የስራ እድል ፈጠራ፣የሀገሪቱን  ምርታማነት በማሳገድ ፣ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን  መተካትና ውጭ ምንዛሬን  በማስገኘቱ ልዩ  ትኩረት መሰጠቱን  ገልጸዋል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥ ስርአትን ለማዘመን በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተቀመጠ  የ100 ቀናት የስራ እቅድ  በመከለስ  ተገልጋዩን ለማርካት በመስራት ላይ ነን ብለዋል፡፡

የኢንቨስትመንት አማራጭን በ100 ቋንቋዎች ማስተዋወቅ የሚያስችል ˝አይጋይድ˝ የተሰኘ ዌብሳት ይፋ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

በኢንቨስትመንት ዘርፉ ከተሰማሩ ተቋማት የጁኒፕር ግላስ ኢንቨስትመንት የኮርፖሬት ግንኙነት   ኃላፊ አቶ ያሬድ ሙሉጌታ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽንጋር ባለፉት ሶስት አመታት በቅርበት መስራታቸውን ሲያስረዱ  ማሽነሪዎችን ከውጭ ለማስገባትም ሆነ በመሬት አቅርቦት  የተሻለ  አገልግሎት  ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡

የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት እንቅስቃሴን ይበልጥ ለማሳደግም ኮሚሽኑ የባለሞያዎቹን አቅም ከአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጋር የሚራመዱበትን አቅም መፍጠር አለበት ብለዋል፡፡

አክለውም በተለይ ከቀረጥ ነጻ የሚገቡ አቃዎችን ዝርዝር መስፈርቶች ቀድሞ ማሳወቅና ከሀይል  አቅርቦት ጋር ያሉ ችግሮች  በተቻለ መጠን መቅረፍ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የሲዜድ ኤ ኢንቨስትመንት  በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ኢንቨስተሮች  በጥምረት ሮተሪና ችቡድ  ለማምረት መቋቋሙን የሚያስረዱት የፕሮጀክቱ የምርት ማኔጀር አቶ ዘሪሁን  ዘውዴ የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ በገቡበት ሶስት አመታት  ለሀገር ውስጥ ገበያ ምርት ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ  ለኢንቨስትመንቱ ውጤታማነት  በየግዜው እየገመገመ ሞያዊ ድጋፍ ማድረጉን በመግለጽ፡፡

መንግስት ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት  የሚፈቅደውን ከቀረጥ ነጻ ማሽነሪዎችና መኪና ብናስገባም ከኢንቨስትመንቱ ስፋት አንጻር ተጨማሪ መኪኖችና የብድር አቅርቦት ለማግኘት  ያሉየህግ ማእቀፎች መሻሻል እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡