የመንግስት እና ኦነግ የሠላም ውይይት በአምቦ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው

102

አዲስ አበባ ጥር 16/2011 በኦሮሞ አባ ገዳዎች ኅብረት የተጀመረው
 በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት እና በኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር /ኦነግ/ መካከል ሠላም ለማውረድ ከትናንት በስትያ የተጀመረው ውይይት ዛሬም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በውይይቱ ላይ አባ ገዳዎች፣ ኦዳ ሲኪዎች፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ የአምቦና አካባቢው ነዋሪዎች፣ የሁለቱ ፓርቲዎችና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አመራር አባላት እየተሳተፉ ነው።

በክልሉ ዘላቂ ሠላም ለማስፈን ሁለቱን ፓርቲዎች ስምምነት ላይ ለማድረስ የቴክኒክ ኮሚቴ መቋቋሙ ይታወቃል።

በመጀመሪያው ውይይት የኦነግ ሊቀ-መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የግንባሩን ታጣቂዎች ጉዳይ ለአባ ገዳዎችና ለኦሮሞ ህዝብ አስረክቤያለሁ ማለታቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም