መቀሌ 70 እንደርታ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ

537

መቀሌ ጥር 14/2011 ዛሬ በተካሄደው የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ የእግር ኳስ ክለብ የኢትዮጵያ ቡና አቻውን አስተናግዶ አንድ ለባዶ አሸነፈ፡፡ 

በትግራይ ዘመናዊ ስታዲዮም በተካሄደው ጨዋታ መቀሌ  70 እንድርታ ያሸነፈበትን  ጎል ያስቆጠረው  በ40ኛው ደቂቃ  ባገኘው የቅጣት ምት  ነው፡፡

ጎሉን ያስቆጠር አማኑኤል ገብረሚካኤል መሆኑ ታውቋል፡፡

የመቀሌ 70 እንደርታ አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይለ በሰጡት አስተያየት”  ጨዋታው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ መጠናቀቁ ደስ ብሎኛል” ብሏል።

የኢትዮጵያ ቡና ስራ አስከያጅ አቶ ስንታየሁ  በቀለ በበኩላቸው  ውድድሩ ስፖርታዊ ጨዋነት የተሞላበት እንደነበር ተናግረዋል፡፡

ጨዋታዋን በሺዎች የሚቆጠሩ ስፖርት አፍቃሪዎች  ተመልክተውቷል፡፡