ጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ ከአፍሪካ ተሳትፎው ተሰናበተ

52

አዲስ አበባ  ጥር 12/2011 ጅማ አባጅፋር እግር ኳስ ክለብ በሞሮኮው ሀሳኒያ አጋዲር እግር ኳስ ክለብ  4 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸነፈ።

ጅማ አባጅፋር በ2018 /2019 የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ ውድድር ትናንት ወደ ሞሮኮ አቅንቶ የመልስ ጨዋታውን ከሀሳኒያ አጋዲር ጋር ባደረገው ጨዋታ አራት ጎሎችን አስትናግዷል።

ባለፈው ሳምንት ጥር 5 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ 1 ለ 0 የተሸነፈው ጅማ አባ ጅፋር በድምር ውጤት 5 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፎ ከኮንፌዴሬሽን ካፕ ውድድር ተሰናብቷል።

ያለፈው ዓመት የኢትዮጵያ ፕሪሚይረ ሊግ አሸናፊው ጅማ አባ ጅፈር የዚህ ዓመት የአፍሪካ መድረክ ጨዋታውን የጀመረው በካፍ ሻምፒዮንስ ሊግ ቢሆንም በግብጹ አል አሃሊ ክለብ ከውድድር መሰናበቱን ተከትሎ ነበር ወደ ኮንፌዴሬሽን ካፑ ዝቅ ብሎ መወዳደር የጀመረው።

ሆኖም በአፍሪካ መድረክ ብዙም ልምድ የሌለው ጅማ አባ ጅፋር በኮንፌዴሬሽን ካፑ ውድድርም ብዙ ርቀት መሄድ ሳይችል በጊዜ ተሰናበቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም