በኦሮሚያ ክልል በ846 ሚሊዮን ብር የመስኖ ልማት ፕሮጄክቶች እየተገነቡ ነው

71

አዳማ ጥር 10/2011 በኦሮሚያ ክልል አርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩ ከተፈጥሮ ዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ የመስኖ ልማት ፕሮጄክቶች ግንባታ 846 ሚሊዮን ብር በሆነ ወጪ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ መስኖ ልማት ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳሙኤል ሁሴን ለኢዜአ እንደገለጹት የፕሮጄክቶቹ  ግንባታ የዝናብ እጥረት በስፋት የሚታይባቸው የክልሉ ዞኖችን መሰረት በማድረግ እየተከነወኑ  የሚገኙ ናቸው፡፡

ይህም  አርሶ አደርና አርብቶ አደር  ከተፈጥሮ ዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ ታሳቢ እንዳደረጉ አመልክተው ገበያ ተኮር  አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን በመስኖ ለማምረት የዘርፉን ስትራቴጅክ እቅድ በመከለስ ወደ ሥራ መግባታቸውን ተናግረዋል።

በተያዘው ዓመት ሁለት መካከለኛ፣ ስድስት ትላልቅና አነስተኛ ጨምሮ 120 የሚሆኑ የመስኖ ልማት ፕሮጄክቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አቶ ሳሙኤል  እንዳሉት የፕሮጄክቶቹ ግንባታ እየተከናወነ ያለው  በባሌ፣ምዕራብ ጉጂ፣ምስራቅና ምዕራብ ሐራርጌ፣ አርሲ፣ቄሌም ፣ሆሮ ጉዱሩና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ውስጥ ነው፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት ውስጥ ግንባታቸው የተጀመረው የመስኖ የፕሮጄክቶቹ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ ነው የታቀደው፡፡

አሁን በተሻለ የክንውን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ያመለከቱን አቶ ሳሙኤል ሲጠናቀቁም 100 ሺህ ሄክታር መሬት የማልማት አቅም እንዳላቸው አስረድተዋል፡፡

ከ200 ሺህ በላይ የሚሆኑት አርሶና አርብቶ አደሮች የመስኖ ልማት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡

በቀጣዩ የበጀት ዓመት256 የሚሆኑ አዳዲስ የመስኖ ልማት ፕሮጄክቶች ግንባታ ለማከናወን የአዋጭነትና የዲዛይን ጥናት በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኙ ተመልክቷል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳባ ደበሌ በበኩላቸው ፕሮጀክቶች ሲጠናቀቁ የክልሉን በመስኖ የመልማት አቅም እንደሚያሳድጉት ተናግረዋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት 1ሚሊዮን 900ሺህ  ሄክታር በመስኖ የማልማት ስራ መጀመሩን አመልክተው  በመስኖ ልማት ስራው ከ2 ሚሊዮን በላይ አርሶ አደሮችና አርብቶ አደሮች የማሳተፍ ስራ እየተከናወኑ መሆኑ ጠቁመዋል፡፡

የሚጠበቀውን ውጤት ለማሳካት የፀረ አረምና የአፈር ማዳበሪያ  እየቀረበ ነው፡፡

በፈጻሚው አርሶ አደር፣አርብቶ አደር፣  በየደረጃው በሚገኙ ባለሙያዎችና አመራሮች ዘንድ የሚታየውን የአመለካከት፣የአቅምና የግብዓት አጠቃቀም ማነቆችን ለመፍታት በቂ ሙያዊ ስልጠና መሰጠቱን አቶ ዳባ አስረድተዋል።

አምና 186 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ከመስኖ ልማት መገኘቱን አስታውሰው በተያዘው  ዓመት 216 ሚሊዮን ኩንታል ለማምረት እየተሰራ መሆኑን ጠቆመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም