የትግራይ ክልል ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባኤውን በመጪው ማክሰኞ ይጀምራል

1250

መቀሌ ጥር  10/2011 የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት የአምስተኛው ዘመን 14ኛው መደበኛ ጉባኤ በመጪው ማክሰኞ ይጀመራል፡፡

በምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነትና የኮንፈርስ አገልግሎት ዋና የስራ ሂደት ባለቤት አቶ ሙሉጌታ ታረቀ ዛሬ እንደገለጹት ጉባኤው ከጥር 14 ቀን እስከ ጥር 19 ለስድስት ቀናት የሚካሔድ ይሆናል።

ጉባኤው  በቆይታው የክልሉን መንግስት  ስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤትና የዋና ኦዲተር ሪፖርት  ላይ ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ከዚሁ በተጨማሪም ለምክር ቤቱ የሚቀርበው የተጨማሪ በጀት ረቂቅና የዳኞች ሹመትን ያጸድቃል፡፡

የማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ስልጣንና ተግባር ለመወሰን ተሻሽሎ የቀረበ አዋጅን ጨምሮ በዘጠኝ ረቂቅ አዋጆች ይጸድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።