የጎንደር ከተማ ወጣቶች የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ተደራጅተው እየሰሩ ናቸው

69

ጎንደር ጥር 9/2011 የጎንደር ከተማ  ወጣቶች የጥምቀት በዓል  በሰላም እንዲከበር ተደራጅተው እየሰሩ መሆናቸውን የከተማው አስተዳደር ፀጥታ ጉዳዮች መምሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው ኃላፊ ኮሎኔል ዘለቀ አለባቸው ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱት ወጣቶቹ ለበዓሉ ወደ ከተማዋ የሚመጡ እንግዶችንና የከተማዋን ነዋሪዎች ሰላምና ደህንነት እየጠበቁ ነው።

ወጣቶች ሥራውን ለማከናወን ስልጠና መውሰዳቸውንም ያመለከቱት ኃላፊው፣ በዓሉ በተሳካ ሁኔታ እንዲከበር ከጸጥታ ክፍሉ ጋር ተቀናጅተው በመሥራት ላይ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ወጣቶቹ ትናንት ምሽት በከተማው ገነት ተራራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የተነሳውን እሳት በማጥፋት ሚናቸው የላቀ እንደነበርም አስታውቀዋል፡፡

በክብረ-በዓሉ ቦታ ህግን የሚተላለፍ ግለሰብም በሚቋቁመው ችሎት ጉዳዩን እንደሚመለከትም ተናግረዋል፡፡

ጎንደር የጥምቀት በዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው ከተሞች አንዷ ስትሆን፣የአገር ውስጥና የውጭ ዜጎችም ይታደሙባታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም