ቤተክርስቲያኗ ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገች

52

ነቀምቴ  ጥር 6/2011 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና ኦሮሚያ ክልል  አዋሳኝ ወረዳዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ለተፈናቀሉ ወገኖች ሁለት ሚሊዮን ብር የሚገመት ፍራሽና ብርድ ልብስ ድጋፍ አደረገች፡፡

የቤተክርስታኗ ፕሬዚዳንት ቄስ ዮናስ ይገዙ  ይህንን 400 ፍራሾችና 1ሺህ ብርድ ልብሶችን  በምሥራቅ ወለጋ ዞን ሳሲጋ ወረዳ  ቀርሳ ሞጆ እና  እና በሎ በሬዳ ቀበሌዎች ለሰፈሩ ወገኖች ትናንት አስረክበዋል፡፡

በዚህ ወቅት እንዳሉት ቤተክርስቲያነው ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን በመገንዘብ  ያደረገችው ድጋፍ የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም፡፡

ወደፊቱም መልሶ ለማቋቋም  አስፈላጊውን ድጋፍ እንደምታደርግ ገልጸዋል፡፡

በበሎ በሬዳ መጠለያ ጣቢያ ከሚገኙ ተፈናቃዮች መካከል  ወይዘሮ ፈቲያ አህመድና ወይዘሮ የሺ መሐሪ   ቤተክርስቲያኗ ላደረገችላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም