ገንዘብ እንደሸቀጥ

1881

ሚስባህ አወል /ኢዜአ/ – ሰሞኑን አንድ ጉዳይ ይዤ የአዲስ አበባ እምብርት ተብሎ ወደሚታወቀው ሰፈር አንድ መስሪያ ቤት ጎራ አልኩኝ ፤ ወደ ፒያሳ አካባቢ ማለት ነው፡፡

ከእቴጌ ጣይቱ ሆቴል አለፍ ብዬ   ብሄራዊ ሎቶሪ ገባሁ፡፡

የብሄራዊ ሎቶሪ ህንጻ ብርቅ በነበረበት ወቅት በሎቶሪዎቹ ላይ ሁሉ ምስሉ ይወጣ ስለነበር ለማንም መንገደኛ ብሄራዊ ሎቶሪ ቅርጫት ሙሉ ብር ከተሸከመችው ሰጎን ጋር ሊያጣው አይችልም፡፡

ጣይቱ ሆቴል እየመሰላቸው ወደ ሎተሪው ቤት ጎራ የሚሉ አዛውንቶች አልጠፉም፡፡

እኔም ወደ ብሄራዊ ሎቶሪ ስሄድ ለመጀመሪያ ጊዜዬ በመሆኑ በር ላይ ያሉ የጥበቃ ሰራተኞችን የህዝብ ግኑኙነት ክፍሉ ወዴት ነው ስል ጠየቅኩ፡፡

ያ! ረጂም ዘመን ካስቆጠረው ህንጻ ጓሮ ወዳለው ዘመናዊ ግን ደግሞ በቅጡ ወዳላለቀ ህንጻ አራተኛ ፎቅ መሩኝ፡፡

ግንታባው ያለማለቁ አንዱ ማሳያ የሆነውን የሊፍቱን ቦታ እያየሁ አራተኛውን ፎቅ በእግሬ ተያያዝኩት፡፡ እዚህ ጋር ነው ጉዳዩ የሚጀምረው፤ በየህንጻዎቹ ኮሪደሮች ቆየት ያሉ ፎቶ ግራፎች በፎቶ ፍሬም ተንጠልጥለዋል፡፡

የኋልዮሽ ዘመንን የሚያሳየው  ፎቶ  ሰዎቹ ብር የተሸከሙ ሳይሆን ብር የተጫናቸው  መስሏል፡፡ ይህ ሁሉ ብር ምን ያደርጉት ይሆን ትሉ ይሆናል? በዛን ዘመን የሚወጣው ከፍተኛ እጣ ግን ከ50 ሺህ የማይዘል ነበር፡፡ ለነገሩ የዛኔው 50 ሺህ ዛሬ በስንት ይሰላ ይሆን፡፡

ድሮ ከአሞሌ የተነሳው የሀገራችን የግብይት ሂደት በብር ተቀይሮ ብርን በጆንያ ተሸክሞ ባንክ መሄድና ማውጣት የተለመደ ክስተት እንደነበር ሲነገር እንሰማለን፡፡

ዛሬ ላይ ስልጣኔው እየዳበረ መጥቶ   ብር መሸከም ቀርቶ አንዷን ብር በምታክል የቼክ ወረቀት ወይም በእጃችን በሚገኝ ሞባይል  አየር ባየር ገንዘባችንን ማንቀሳቀስ የተለመደ ሆኗል፡፡

እዚያ ብሄራዊ ሎቶሪ ኮዛሬ ላይ ስልጣኔው እየዳበረ መጥቶ   ብር መሸከም ቀርቶ አንዷን ብር በምታክል የቼክ ወረቀት ወይም በእጃችን በሚገኝ ሞባይል  አየር ባየር ገንዘባችንን ማንቀሳቀስ የተለመደ ሆኗል፡፡ሪደር ግርግዳዎች ላይ ካገኘሁዋቸው አስገራሚ መረጃዎች መካከል የእውቁ ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ትንቢት ተናጋሪነት ሳብ አደረገኝና ግድግዳው ላይ ያለውን ጽሁፍ ገረፍ ገረፍ አድርጌ አነበብኩት፡፡

ዛሬ ላይ ስልጣኔው እየዳበረ መጥቶ   ብር መሸከም ቀርቶ አንዷን ብር በምታክል የቼክ ወረቀት ወይም በእጃችን በሚገኝ ሞባይል  አየር ባየር ገንዘባችንን ማንቀሳቀስ የተለመደ ሆኗል፡፡

የጳውሎስ ንግግር እንደወረደ ሲታይ ትንቢት ተናጋሪ ያስመስለዋል፤ ምክንያቱም ዛሬ ላይ ብሄራዊ ሎቶሪ የእጣው ከፍታ አስር ሚሊዮን ደርሷልና!!

“ሎተሪ እጣ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሲወጣ አውቃለሁ፡፡ለጋዜጣ ዜና ለመውሰድ ስል እሄድ ነበር፡፡ ከዚያም አንድ ሁለት ዓመት ከቆየሁ በኋላ ሰዎች ለዳኝነት ለታዛቢነት ተመርጠው የገቡ ጊዜ እኔም አንዱ ሆኜ እስከ 66 ሰርቻለሁ’’ ነው ያለው ጋዜጠኛው፡፡

“እና…በጣም የማደንቀው ነገር ነበር፤ የማደንቀው የሰዎቹን ታማኝነት ብቻ ሳይሆን የማሽኑ ዕጣ አወጣጥ ምንም የማያወላውልና የማያዳላ በመሆኑ ነው፡፡”  እያለ የሚቀጥለው የተንባዩን የጋዜጠኛ ጳውሎስ ጽሁፍን እያነበቡ ሲወርዱ የሚያገኙት ትንቢታዊ መልዕክቱን ነው፡፡

ታድያ ይህንንም እንዳለ ሳወርደው እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

“እኔ የሚኮረኩረኝ ለማሳቅ ያህል የሚሞክረኝ የዕጣ ክፍያ እድገቱ ሚሊዮን ደርሶ ዕጣው ለኔ ቢደርሰኝ ምን አደርገዋለሁ ብየ ነው፡፡ አንድ ሚሊዮን ብር ቀላል አይደለም በበኩሌ በእድሜዬ ቆጥሬ አላውቅም ማንም ሀብታም ቢሆን ሚሊዮን ቆጠርኩ የሚል የለም፤ የባንክ ሰራተኞችም ቢሆኑ ሚሊዮን የሚደርሱ አይመስለኝም፡፡ በሂሳብ ነው፡፡ ሚሊዮን ቀላል ነገር አይደለም፡፡

“በውነቱ ይሄ ነገር ሳላረጅና ሳልሞት የሎተሪ እጣ ክፍያ ሚሊዮን ቢደርስ ደስ ይለኝ ነበር፡፡ እና….አሁንም ቢሆን አልጠራጠርም፡፡ ወይም እደርስበት ይሆናል፡፡”

ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ ህይወቱ በምታልፍበት በዚያን ወቅት ብሄራዊ ሎቶሪ ምናልባት የእጣውን ዋጋ አንድ ሚሊዮን አድርሶት ይሆናል፡፡

አሁን ባለንበት ዘመን ግን አንድ ሚሊዮን ይህን ያህል የከበደ አይደለም፡፡ ለአብነትም አንድ ምሳሌ ላካፍላችሁ ገና ሪፖርተር ሆኜ ስቀጠር በ12 ሚሊየን ብር የተገነባ የዱቄት ፋብሪካ ስራ ጀመረ፡፡ በሚል አንድ ዜና ለማስተላለፍ የዜና አዘጋጅ/አርታኢን ሳስፈቅድ “ፋብሪካ ነው ወፍጮቤት በ12 ሚሊዮን ብር የሚገነባው ” ብሎ ጠየቀኝ፡፡ አሁን ያለው የብር የመግዛት አቅም ይሆን ወይስ የሀገሪቱ እድገት ያመጣው ነው ብዬ ከራሴ ጋር መነጋገር ጀመርኩ፡፡

እንግዲህ ጋዜጠኛ ጳውሎስ ውድ የሆነበት ያቺ አንድ ሚሊዮን ብር ዛሬ ዛሬ ተራ ከመሆኗ ባለፈ በብዙ እጥፍ አድጋ በጆንያ እየተጠቀለለች በጓሮ በር ልትወጣ ስትል በቁጥጥር ስር ዋለች የሚለው የዘመኑ የተለመደ ወሬ ሆኗል፡፡

ከጉዳዩ ጋር የተያያዘ በቅርቡ የሰማሁት ዜናም እንዲህ ይላል “በአፋር አካባቢ በአንድ ግለሰብ በሶስት ጆንያ ተጭኖ ሲጓጓዝ የነበረ 10 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር በቁጥጥር ስር ዋለ” የሚልነው፡፡

አስታውሱት ከዛሬ 30 ዓመት በፊት በ1981 ዓ.ም ጋዜጠኛ ጳውሎስ የባንክ ሰራተኞች እንኳን ሚሊዮን አይቆጥሩም ነበር ያለን፡፡ ዛሬ ግን ብሩ የወጣው ደግሞ ከባንክ ነው፡፡ ዛሬ ላይ የባንክ ሰራተኞች አንድ ሚሊዮን አይደለም ሚሊዮኖች በመቁጠር ላይ ናቸው፡፡

በአሻጥር ብራችን በቁሙ ከሀገር መኮብለሉ ሁላችንንም ሳይስደነግጥ አልቀረም ! የሚወጣበት መንገድ ደግሞ በአየር መንገድና በተለያዩ ቦታዎች እንደ ቀልድ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሲዘዋወር በፖሊስ መያዙ ንግድ ባንካችን ውስጥ ምን ቀረ ሳያስብል አልቀረም፡፡

ባለፈው ታህሳስ ወር ብቻ ወደ አዳማ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 90 ሺህ ዶላር እንዲሁም በአሶሳ 12ሺህ ዶላር መያዙን ሰምተናል፡፡ ይሄ በህግ በቁጥጥር ስር የዋለ ነው፡፡ ያልተያዘውማ ቤት ይቁጠረው ለከንቱ አላማ  የዋለውስ ?

በህዳር ወርም 147 ሺህ ዶላር ተይዞ በትንሹ ከ3 ሚሊዮን 964 ሺህ ብር ገቢ መደረጉን ኢዜአ ከሰራቸው ዜናዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡

በቅርቡ የፌደራል ፖሊስ በድረገጹ ያስነበበንን መረጃ ደግሞ ላካፍላችሁ፡፡

ካለፈው ከሀምሌ 2010 እስከ ህዳር 2011 ዓ.ም በፈጥኖ ደራሽ ዳይሬክቶሬት ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበርና በመቀናጀት 73 ሚሊዮን 192 ሺህ 670 የኢትዮጵያ ብር፣ 6510 ዩሮ፣ 36 ሺህ 150 ዶላር፣ 127 ሺህ 760 የደቡብ ሱዳን ገንዘብ እና 21 ሺህ የሱዳን ገንዘብ ይዞ ለጉምሩክ ገቢ ማድረጉን አስፍሯል፡፡

ህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር የሚፈፀምባቸው አካባቢዎች ጅግጅጋ፣ሰመራ፣ቴፒ፣መተማ መስመር፣ ኮንሶ፣ ዳንጉር፣ ቶጎው ጫሌ፣ አልማሀል እና ድችቶ አካባቢዎች እንደሆኑም ነው በታህሳስ ወር አጋማሽ የፌዴራል ፖሊስ ያወጣው መግለጫ ያስነበበው፡፡

ሀገራችን በራስ አቅም ልትገነባቸው የያዘቻቸው በርካታ ትላልቅ ፕሮጀክቶች በዚህና መሰል ተግባራት ተሰናክለው ሲቀሩ ማየትም ያማል፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ የሚባክን ብር በፍጥነት እያደገ  የሀገራችን እድገት ደግሞ በተቃራኒው እንዳይሆን አሁን የተጀመረው ህጋዊ እርምጃና ሌሎች የማስተካከያ ሥራ መሰራት ግድ ይላል፡፡

ሺዎች  ውድ ፣ ሚሊኖች ብርቅ የነበሩበትን የጋሽ ጳውሎስ ዘመን አልፈን ዛሬ ሚሊዮኖች እንደሸቀጥ በጆንያ የሚዘዋወሩበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡

ይህን ለማስተካከል ከታች ጀምረን በሥነ-ምግባር የታነፀ ትውልድ በመፍጠሩ ላይ ተግተን መሥራት ዋናው ተግባራችን ሊሆን ይገባል መልዕክቴ ነው፡፡