ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ጎንደር ከተማ ሲገቡ አቀባበል ተደረገላቸው

796

ጎንደር ጥር 4/2011 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትረያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ዛሬ ጎንደር ከተማ ሲገቡ አቀባበል ተደረገላቸው፡፡

ለፓትረያርኩ  በጎንደር መስቀል አደባባይ በመገኘት አቀባበል ያደረጉላቸው የአካባቢዎች ነዋሪዎችና የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ናቸው፡፡

ከንቲባው  ዶክተር ሙሉቀን አዳነ በዘ ወቅት  ባሰተላለፉት መልዕክት “ለሩብ ምዕተ ዓመት በግዞት ቆይተው በሊቀ ጵጵስና ሲያገለግሉት ወደ ነበሩት ህዝብ መጥተው እንደገና አገልግሎት መስጠት መጀመራቸው የለውጡ አንዱ አካል ነው”  ብለዋል፡፡

ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት፣ ካህናትና ዲያቆናት እንዲሁም ሊቃነ ጳጳሳት በጎንደር አካባቢ ያለ የወንድማማቾች መጎዳዳት እንዲቆም ተግተው እንዲፀልዩና እንዲያስተምሩም ጠይቀዋል፡፡

የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ለፓትረያርኩ ያላቸውን ድጋፍና አክብሮት አደባባይ በመውጣት ገልጸዋል፡፡

ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆርዮስ ፓትረያርክ ሊቃነ ጳጳስ ዘኢትዮጵያ ጋር ሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግዛት አብዩ እና የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ አስረስ ተገኝተዋል፡፡