በሶማሌ ክልል ከአንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን በላይ ህጻናት የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ተሰጠ

56

ጅግጀጋ ጥር 2/2011 በሶማሌ ክልል ከአምስት ዓመት በታች ዕድሜ ለሆኑ ከ1 ነጥብ  1ሚሊዮን በላይ ህጻናት የፖሊዮ በሽታ መከላከያ ክትባት ተሰጠ፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ የተላፊና ውሃ ወለድ በሽታዎች መቆጣጠሪያ ሥራ ሂደት መሪ አቶ ሲራጅ አደን የቤት ለቤት ክትባት ላለፉት 5 ቀናት በሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች መሰጠቱን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልጸዋል።

በዘመቻው ላይ ከ6 ሺህ የሚበልጡ ባለሙያዎች፣ ተቆጣጣሪዎችና መንገድ መሪዎች መሳተፋቸውንም ተናግረዋል።

የክልሉ የአርብቶ አደር ጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞችና የጤና ባለሙያዎች ቤት ለቤት በመንቀሳቀስ አገልግሎቱን መስጠታቸውን አመልክተዋል።

እንደ ኃላፊው ገለጻ ክትባቱ  የተሰጠው በሶማሊያ የታየው በሽታ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ  አስቀድሞ ለመከላከል ነው፡፡

ለፕሮግራሙ ስኬት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር፣ የዓለም ጤና ድርጅትና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ አድርገዋል ብለዋል ።

በጅግጅጋ ከተማ ከተማ ቀበሌ አራት ነዋሪ ወይዘሮ ሑኩን ሐሰን በሰጡት አስተያየት የክትባቱን አስፈላጊነት በመገንዘብ ልጆቻቸውን ማስከተባቸውን ተናግረዋል።

ሌላዋ የቀበሌ አምስት ነዋሪ ወይዘሮ ሩቅያ ኡመር በየወቅቱ በዘመቻና በጤና ተቋማት በሚሰጠው የክትባት አገልግሎት ልጆቻቸውን በማስከተብ ከበሽታው ስጋት ነፃ እንዳደረጓቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም