የግንቦት 20 ድሎችን ጠብቆ ለትውልድ ለማስተላለፍ እንደሚሰራ በትግራይ የታጋይ ሰማዕታት ልጆች ማህበር አስታወቀ

2139

መቀሌ ግንቦት 17/2010 በመስዋዕትነት የተገኙትን የግንቦት 20 ድሎች በመጠበቅ ለትውልድ ለማስተላለፍ የሚጠበቅበትን እንደሚያከናውን በትግራይ የታጋይ ሰማዕታት ልጆች ማህበር አስታወቀ።

የታጋይ ሰማዕታት ቤተሰብ ማህበር 27ኛውን የግንቦት 20 የድል በዓል አስመልክቶ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው ማህበሩ ለድሉ መሰረት የሆኑትን ታጋዮች ታሪክ ለትውልድ ለማውረስ በትኩረት ይሰራል።

በታጋይ ሰማዕታት የሕይወት መስዋዕትነት የተገኙ የግንቦት ሃያ ድሎች ተገቢ ክብር እንዲያገኙና በዘላቂነት እንዲታወሱ ማድረግም ማህበሩ ከተቋቋመበት ዓላማ አንዱ መሆኑን በመግለጫው አስታውቋል፡፡

በመጪው ሰኞ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የግንቦይ ሃያ በዓልን ምክንያት በማድረግም ማህበሩ በነገው ዕለት በመቀሌ ከተማ አገር አቀፍ  የፓናል ውይይትና የሙዚቃ ኮንስረት ማዘጋጀቱ ተመልክቷል።

በመግለጫው እንደተገለጸው በፓናል ውይይቱ  ላይ ምሁራን፣ ነባር ታጋዮች፣ ፖለቲኮኞችና የአገር ሽማግሌዎች ተሰታፊ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።