የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ከስልጣን ለመልቀቅ ደብዳቤ አስገቡ

77
ታህሳስ 12/2011 የአሜሪካ የመከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ከስልጣን መልቀቂ ደብዳቤ ለትራምፕ አስተዳደር አስገብተዋል። ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው ጂም ማቲስ በመጪው የካቲት ወር በክብር ይሰናበታሉ የሚል ምላሽ ሰጥተዋል። አሜሪካ ጦሯን ከሶሪያ እንደምታስወጣ ይፋ ባደረገች በአንድ ቀን ልዩነት ነው የመከላከያ ሚኒስትሩ የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤ ያስገቡት። የሀገሪቱ ጦር ከሶሪያ መውጣት በትራምፕና በመከላከያ ሚኒስትሩ መካከል የፖሊሲ ልዩነት ፈጥሮ ማቲስ ስልጣን ለመልቀቅ እንደተገደዱ በርካቶች እየተናገሩ ነው። ትራምፕ ስልጣን የሚለቁትን ማቲስን ተክቶ የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ማን ሊሆን እንደሚችል እስካሁን ባይጠቁሙም በቅርቡ ይሾማል ነው ያሉት። የመከላከያ ሚኒስትሩ ጂም ማቲስ በመልቀቂያ ደብዳቤያቸው አሜሪካ አጋሮቿን በክብር  ማስተናገድና ሁሉንም የጦር ኃይሏን ለጋራ የመከላከል መርህ መጠቀም እንደሚገባት ለትራምፕ በቀጥታ ጽፈዋል። “በእነዚህና መሰል ጉዳዮች የመከላከያ ሚኒስትሩን ሀሳቦችና እይታዎች የማግኘት መብት አለዎት ሲሉ ለትራምፕ የገለጹላቸው ማቲስ ከስልጣኔ መልቀቄ ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ” ብለዋል። ምንጭ፦ቢቢሲ  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም