በጋምቤላ ክልል የወባ በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል የመድኃኒት ርጭትና የአጎበር ስርጭት እየተካሄደ ነው

70
ጋምቤላ ግንቦት 17/2010 በጋምቤላ ክልል የክረምቱን መግቢያ ተከትሎ ሊጨምር የሚችለውን የወባ በሽታ  አስቀደሞ ለመከላከል የመድኃኒት ርጭትና የአጎበር ስርጭት እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡ የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ እንዳስታወቀው እየተካሄደ ያለው  የመከላከሉ ስራ ከ422 ሺህ በላይ ህዝብ  ከበሽታው ለመጠበቅ የሚያስችል ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት  የፀረ- ወባ ኬሚካል  ርጭት በሁሉም የክልሉ ወረዳዎች በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ የቢሮው ኃላፊ  ዶክተር ኡማን አሙሉ ለኢዜአ ገልጸዋል፡፡ የክልሉ ሁሉም ወረዳዎች ለወባ በሽታ የተጋለጡ መሆናቸውን ያመለከቱት ኃላፊው የክረምቱ ወቅት ከመድረሱ በፊት በሽታን አስቀድሞ መካለከል የሚያስችሉ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። አሁን ላይ የጋምቤላ ከተማ አስተዳደን ጨምር በክልሉ በሚገኙ 14 ወራደዎች ከ145 ሺህ በሚበልጡ ቤቶች ላይ  ከዚሁ  ሳምንት ጀምሮ የፀረ- ወባ ኬሚካል እየተረጨ  ይገኛል ። እንዲሁም በክልሉ  ከ253 ሺህ የሚበልጡ የወባ ትንኝ መከለካከያ አጎበሮች ክረምቱ ከመድረሱ በፊት ለህብረተሰብ መሰራጨቱን አስታውቀዋል። " በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች የህዝቡን ግንዛቤ በማሳዳግም ውሃ የሚያቁሩ የወባ ትንኝ መራቢያ አካባቢዎችን  እንዲጸዳ እየተደረገ ነውም " ብለዋል። በተጨማሪም በበሽታው የሚጠቁ ሰዎች ህክምና በአቅራቢቸው የጤና ተቋማት  የፀረ-ወባ ፈዋሽ መድኃኒት እንዲያገኙ በበቂ ሁኔታ መመቻቸቱን ጠቁመዋል። ጋምቤላ ከተማ አስተዳደር የፀረ- ወባ ኬሚካል ርጭት አስተባባሪ አቶ ክንፍ ቆጭቶ በበኩላቸው የወባ በሽታን ለመከላከል የተጠናከር የፀረ- ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት፣ የአጎበር ስርጭታና ሌሎችም ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም በጋምቤላ ከተማ  ከ12 ሺህ  በሚበልጡ ቤቶች ላይ የፀረ-ወባ ኬሚካል ርጭት ለማካሄድ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ መገባቱን ገልጸዋል። መኖሪያ ቤታቸው የፀረ- ወባ ኬሚካል በመረጨቱና የወባ ትንኝ መከላከያ አጎበርም የደረሳቸው በመሆኑ የበሽታው ስጋት እንደሌለባቸው የተናገሩት ደግሞ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪው አቶ ኝጌዎ ኦቦንግ ናቸው። በሽያውን ለመከላከል የወባ ትንኝ መራቢያ ቦታዎችን ቤተሰባቸወን ጭምር በማሰማራት እያጸዱ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሌላው የከተማው ነዋሪ ወይዘሮ ኡጎቶ ኦኬሎ በበኩላቸው የወባ በሽታን መከላከል የሚቻለው በአካባቢ ጽዳት፣ በፀረ ወባ ኬሚካል ርጭትና የወባ ትንኝ መከላከያ አጎበርን በመጠቀም መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በተለይም የፀረ- ወባ ትንኝ ኬሚካል ርጭት የወባ ትንኝ ስለሚጠፉና ጤንነታቸው ስለሚጠበቅ ቤታቸውን እያስረጩ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም