ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ ከሱዳን መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ

529

ካርቱም ታህሳስ 11/2011 በሱዳን ይፋዊ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከሱዳን መንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያዩ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ሞቶዛ ሙሳ፣ ከተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኡስማን ሞሃመድ ዩሱፍ ኪቢር እና ከምክትል ፕሬዚዳንት ባክሪ ሃሰን ሳላህ ጋር በኢትዮጵያና ሱዳን ሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ መክረዋል።

ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎቹ ጋር በአገሮቹ ሁለንተናዊ ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት እንደተወያዩ ታውቋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትናንትናው ዕለት ከሱዳን ፕሬዚዳንት ኦማር ሐሰን አል-በሽር ጋር በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደ ተሻለ ደረጃ ማሸጋገር ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ማድረጋቸው ይታወቃል።