በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ነፃ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ሕክምና አገልግሎት ሊሰጥ ነው

909

አሶሳ  ታህሳስ 10/2011 በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ነፃ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ህክምና አገልግሎት እንደሚሰጥ የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ አስታወቀ።

በክልሉ ከአራት ወራት ዕድሜ ጀምሮ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ችግር ያለባቸው ግለሰቦች ከታህሳስ 12-14/2011 ድረስ አገልግሎቱ ይሰጣቸዋል።

የቢሮው የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ኃላፊ አቶ ዋጮ ዋቡልቾ ለኢዜአ እንዳስታወቁት ታካሚዎቹ ለሦስት ቀናት በአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ነፃ የቀዶ ህክምና አገልግሎት ያገኛሉ፡፡

አገልግሎቱን የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታልና ሐረር ፕሮጀክት በተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ትብብር  እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡

ኅብረተሰቡ አገልግሎቱ በክልሉ የሕክምና ተቋማት በመደበኛነት በማይሰጠው  አገልግሎት እንዲጠቀምበት ኃላፊው አሳስበዋል፡፡

በኢትዮጵያ አንድ ሺህ አንድ መቶ የከንፈርና ላንቃ መሰንጠቅ ችግር ያላባቸው ወገኖች በሐረር ፕሮጀክት አማካይነት ሕክምና ማግኘታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ።