ሳዑዲ አረቢያ በህክምና ስህተት ጉዳት ለደረሰበት ኢትዮጵያዊ ታዳጊ 3 ሚሊየን ሪያል ካሳ ከፈለች

81
አዲስ አበባ ግንቦት 17/2010 ሳዑዲ አረቢያ ውስጥ በህክምና ስህተት ጉዳት ደርሶበት ለዓመታት የቆየው ኢትዮጵያዊ ታዳጊ መሀመድ አብዱላዚዝ 3 ሚሊየን የሳዑዲ ሪያል ካሳ እንደተከፈለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ለሀገሪቱ መንግስት ያቀረቡት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቶ የካሳ ክፍያው ለቤተሰቦቹ ተፈጽሟል፡፡ ታዳጊውን በሁለት ሳምንት ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ በመመለስ ህክምናውን እንዲከታተል በውጭ ጉዳይና በጤና ጥበቃ ሚኒስቴሮች አማካኝነት ዝግጅት እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡ ታዳጊው መሃመድ አብዱላዚዝ ከ12 ዓመት በፊት ባጋጠመው የመተንፈሻ እክል አፍንጫው ላይ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ነበር ወደ ጂዳ ሆስፒታል ያመራው።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም