የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

104
አዲስ አበባ ሚያዝያ 24/2010 የጀርመኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሄኮ ማስ ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ እንደሚገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ሄኮ ማስ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ ጋር ተገናኝተው በሁለትዮሽ እና በአካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ያደርጋሉ፡፡ ሚኒስትሩ በቆይታቸው የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሞሳ ፋኬ ማሃማትን ያነጋግራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ጀርመን  በልማት ትብብር፣ በኢንቨስትመንት ዘርፎች እና በንግድ ተደራሽነት ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት ጠንካራ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝት የሁለቱን አገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ ያጠናክረዋል፡፡ የጀርመኗ ቻንስለር አንጌላ ማርኬል በጥቅምት 2008 ዓ.ም ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም