ኢትዮጵያለጎረቤት  ሀገራት ከሸጠችው  የኤሌክትሪክ ኃይል ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ  አገኘች

86
ታህሳስ 3/2011 የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለሱዳንና ጅቡቲ ካቀረበው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ 28 ሚሊየን 414 ሺህ 752 ዶላር ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል። የተቋሙ የማርኬቲንግና ቢዝነስ ዲቨሎፕመንት ቢሮ  እንደገለጸው ገቢው የተገኘው ከሠኔ 2010 እስከ ጥቅምት 2011 ዓ.ም ባሉትአምስት ወራት ውስጥ ነው፡፡ ጅቡቲ 17 ሚሊየን 501 ሺህ 484 ዶላር የኃይል ግዥ  በመፈፀም ከፍተኛውን ድርሻ  ስትወስድ ቀሪው 10 ሚሊየን 913 ሺህ 259 ዶላርደግሞ ከሱዳን የተገኘ ነው ብሏል። ኢትዮጵያ ታዳሽ የኤሌክትሪክ  ኃይል በማልማት በምስራቅ  አፍሪካ ኢኮኖሚያዊ ትስስር  ለመፍጠር እየሰራች ሲሆን ለጅቡቲና ሱዳንበዓመት በአማካይ ከ150 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል እየሸጠች መሆኗን ቢሮው ገልጻል፡፡ በኤሌክትሪክ ኃይል ካላት እምቅ አቅም ለመጠቀምና የሁለትዮሽ የኃይል ትስስር ለመጀመር ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ፍላጎትከማሳየት ባሻገር ወደ ስምምነት እየመጡ ነው ብሏል። ኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜያት ውስጥ ከሶማሌ ላንድ፣ ኬንያ፣ ታንዛኒያ እና ደቡብ ሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ትስስር ለመፍጠርየሁለትዮሽ ግንኙነት በማድረግ ላይ ትገኛለች። በዚህም በቀጣይ ለእነዚህና ለሌሎች ሃገራት በቂ ኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የውጪ ምንዛሬ ከሚያስገኙ  ዘርፎች መካከል አንዱለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ነው የተገለጸው።በአሁኑ ሰዓትም ኢትዮጵያንና ኬንያን በኃይል ልማት ለማስተሳሰር ባለ 500 ኪሎ ቮልት ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመርግንባታ እየተከናወነ ነው፡፡ ኢትዮጵያ በ2010 በጀት ዓመት ለሱዳንና ጅቡቲ ካከናወነችው የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ከ75 ሚሊየን ዶላር በላይ ማግኘቷይታወሳል፡፡ ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ድረ-ገጽ
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም