ለጅማ-አጋሮ-ዴዴሳ ወንዝ ድልድይ የመንገድ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

2017

ጅማ ህዳር 29/2011 ከጅማ-አጋሮ-ዴዴሳ ወንዝ ድልድይ ድረስ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ለመገንባት በኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ጅቡቲ መሪዎች የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር እና ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ ጋር በመሆን ዛሬ የመሰረት ድንጋዩን አስቀምጠዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የመሰረት ድንጋይ መቀመጡ መልካም ቢሆንም የሚያኩራራ ሳይሆን የበለጠ እንድንሰራ የሚያነሳሳ ነው ብለዋል።

ከ79 ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያለው መንገድ በቻይናው ሬል ዌይ ኮንስትራክሽን የሚገነባ ሲሆን ከ1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ይፈጃል።

ወጪው በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ሲሆን ግንባታው በሶስት ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል።