የጅማ-አጋሮ-ዲዴሳ ወንዝ ድልድይና የአስፋልት መንገድ ግንባታ ሊጀመር ነው

128
ጅማ ህዳር 29/2011 የጅማ-አጋሮ-ዲዴሳ ወንዝ ድልድይና የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ሊጀመር ነው። ዛሬ በጅማ ከተማ በሚኖረው የግንባታው ማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በመገኘት መልእክት እንደሚያስተላልፉም ይጠበቃል። መንገዱ 79 ነጥብ 07 ኪሎ ሜትር ርዝመት የሚሸፍንና በቻይናው ሬል ዌይ ኮንስትራክሽን ድርጅት የሚገነባ ሲሆን፣ ከ 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባ ነው። ግንባታው 3 ዓመት ተኩል የሚወስድ ሲሆን ወጪው በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ይሆናል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም