በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ግቢ ውስጥ ግዙፍ መካነ እንስሳት ሊገነባ ነው

112
አዲስ አበባ ህዳር 28/2011 በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ግቢ ውስጥ ግዙፍ መካነ እንስሳት ሊገነባ መሆኑ ተገለጸ። መካነ እንስሳው (Zoo) 245 የሚጠጉ የተለያዩ እንስሳቶችን እንደሚይዝም ታውቋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ 13ኛውን የብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በዓልን አስመልክቶ ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች የመጡ ህጻናት ተማሪዎች ጽህፈት ቤታቸውን በጎበኙበት ወቅት ስለ መካነ እንስሳው ማብራሪያ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚነሰትሩ እንዳሉት፤ መካነ እንስሳው በቀጣይ ዓመት መስከረም ወር ስራ ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል። ለተለያዩ ጉዳዮች ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የሚመጡ ተማሪዎችና ሌሎች እንግዶች መካነ እንስሳውን እንደሚጎበኙም አክለዋል። መካነ እንስሳው ኢትዮጵያ በብዝሃ ህይወት የበለጸገች አገር መሆኗን  በቀላሉ ለማስገንዘብ እንደሚረዳም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ የበርካታ ብርቅዬ እንስሳ መገኛ ብትሆንም ይህን ሃብት የሚመጥን መካነ እንስሳ  እንደሌላት በተደጋጋሚ ሲነሳ መቆየቱ ይታወሳል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም