በትግራይ ክልል በትምህርት ቤቶች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እየተሰጠ ነው

95
መቀሌ ህዳር 27/2011 በትግራይ በሚገኙ 2 ሺህ 179 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች  የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ  ክትባት መሰጠት መጀመሩን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። በቢሮው የክትባት ባለሙያ አቶ ሰለሞን አሰፋ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከትላንት ጀምሮ እየተሰጠ ባለው ክትባት ዕድሜያቸው 14 ዓመት የሞላቸው ከ60 ሺህ በላይ ልጃገረድ ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ። "በሽታው በአብዛኛው በልቅ የግብረ ስጋ ግንኙነት የሚከሰት በመሆኑ ልጃገረዶች የግብረ ስጋ ግንኙነት ከመጀመራቸው በፊት ክትባቱን መሰጠት አስፈልጓል " ብለዋል ። ክትባቱ ልጃገረዶቹ በሌሎች ተላላፊ በሽታዎች እንዳይጠቁ ማገልገሉን  ተናግረዋል። በመቀሌ ከተማ የዓይደር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሰባተኛ ክፍል ተማሪ ታዳጊ ወጣት አበባ አብርሃ "ከበሽታው እራስን ለመከላከል መሆኑን በማመኔ ክተባቱን ወስጃለሁ " ብላለ፡፡ "ከጤና ባለሙያዎች በተሰጠኝ ግንዛቤ  መሰረት ክትባቱን ወስጃለሁ" ያለችው ደግሞ በመቀሌ የኢትዮ-ቻይና ትምህር ቤት ተማሪ ህሊና የማነ ነች።          
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም