የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከዛሬ ጀምሮ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

81
አዲስ አበባ ህዳር 27/2011 የጣሊያን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢማኑኤላ ዲልሪ ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀናት በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ያደርጋሉ። በጉብኝታቸው ከውጭ ጉዳይ ፣ ከገንዘብ ፣  ከንግድ እና ግብርና ሚኒስቴሮች የሥራ ኃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። በአዲስ አበባ የሚገኘውን የጣሊያን ባህል ማዕከልና የዶንቦስኮ የወጣቶች ማዕከልና ትምህርት ቤትን እንዲሁም በአገሪቱ መንግስት የሚደገፈውን የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ተቋም እንደሚጎበኙም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ ከሚኖሩ የጣሊያን ማህበረሰብ አባላትና ባለሃብቶች ጋር ለመወያየትም መርሃ-ግብር ተይዞላቸዋል። የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ጥቅምት 2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም