የአዲስ አበባና አንካራ ከተሞችን እህትማማችነት የሚያጠናክር ውይይት ተካሄደ

113
አዲስ አበባ ህዳር 27/2011 የአዲስ አበባና የአንካራ ከተሞችን እህትማማችነት ማጠናከር የሚያስችል ውይይት በቱርክ ተካሄደ። በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ተመስገን ከአንካራ ከተማ ከንቲባ ዶክተር ሙስጦፋ ቱና ጋር ተወያይተዋል። የሁለቱ ከተሞች ግንኙነት በሚጠናከርበትና በአንካራ አዲስ በሚሰራው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግንባታ ዙሪያም መክረዋል። ኢትዮጵያና ቱርክ ከኦቶማን ኢምፓየር ጀምሮ የዘለቀ ወዳጅነት ያላቸው አገሮች ናቸው። የአዲስ አበባና አንካራ እህትማማችነትና ወዳጅነት የተጀመረው እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር 2017 መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢዜአ የላከው መግለጫ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም