የታዳጊ ወጣቶች የቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና ተጀመረ

71
አዲስ አበባ ህዳር 24/2011 ሁለተኛው አገር አቀፍ የስፕራይት ቦለርስ የታዳጊ ወጣቶች የቅርጫት ኳስ ሻምፒዮና ዛሬ በአዲስ አበባ ተጀመረ። በታዳጊ የወጣቶች ሻምፒዮናው በወንዶች ሰባት ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉ ሲሆን በሴቶች ከሶማሌ ክልል በስተቀር ሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ተካፋይ ናቸው። ውድድሩ በአዲስ አበባ ራስ ኃይሉ የስፖርት ማዕከልና ትንሿ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን በሁለት ምድብ ተከፍሎ ይካሄዳል። በወንዶች ምድብ ''ሀ'' ጋምቤላ፣ አፋር፣ ኦሮሚያና ድሬዳዋ ተደልድለዋል። በምድብ ''ለ'' ደግሞ፣ ሱማሌ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ሐረሪ፣ ደቡብ  ክልልና  አዲስ አበባ ተደልድለዋል። በሴቶች በምድብ ''ሀ '' ጋምቤላ፣ አፋር፣ ኦሮሚያና ድሬዳዋ የተደለደሉ ሲሆን በምድብ ''ለ'' አዲስ አበባ፣ ቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ሐረሪና ደቡብ ተደልድለዋል። የውድድሩ ተካፋዮች ዕድሜቸው ከ17 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ሲሆኑ ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜ ህዳር 29 ቀን 2011 ዓ.ም ፍጻሜውን ያገኛል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም