ካሜሩን የ2019 የአፍሪካ ዋንጫ አታስተናግድም -ካፍ

92
ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ካሜሩን የ2019 አፍሪካ ዋንጫን በሀገሯ የማስተናገድ መብት መነጠቋን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ ካሜሩን በመጪው ሰኔ ሊካሄድ ቀጠሮ የተያዘለትን የአፍሪካ ዋንጫ የማስተናገድ መብት የተነጠቀችው የዋንጫ ውድድሩን ለማሳናዳት በቂ እና አሳማኝ ዝግጅት ባለማድረጓ ነው ተብሏል፡፡
በመሆኑም የአዘጋጅነቱ መብት ለአዲስ ሀገር በዚህ ወር መጨረሻ እንደሚሰጥ ትናንት ጋና አክራ ላይ በተደረገው የካፍ ስራ አስፈጻሜ ኮሚቴ ረዥም ስብሰባ መወሰኑን ነው የተነገረው፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን የዘንድሮው የ2019 አፍሪካ ዋንጫ ለመጀመሪያ ጊዜ 24 ብሄራዊ ቡድኖች እንዲካፈሉበት መወሰኑ ይታወሳል፡፡ ካሜሩን የአፍሪካ ዋንጫ የወቅቱ አሸናፊ ስትሆን ግብጽን በመርታት በታሪኳ ለ5ኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ባለቤት መሆኗ አይዘነጋም፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ አዲስ አዘጋጅ ሀገር ጥያቄውን እስከ ወሩ መጨረሻ ድረስ የማድረስ ጊዜ እንዳለው ገልጸዋል፡፡ ምንጭ፣ ቢቢሲ ስፖርት
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም