የቤጉህዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ተጀመረ

96
አሶሳ ህዳር 22/2011 የቤንሻንጉል ጉምዝ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ቤጉህዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጀመረ። የፓርቲው  ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ዚያድ አብዱላሂ ለኢዜአ እንደተናገሩት የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ በአሶሳ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል። በስብሰባው የክልሉ የፀጥታ ሁኔታ ዋነኛ አጀንዳ እንደሆነ ነው  ኃላፊው የገለፁት፡፡ እያንዳንዱ የማዕከላዊ ኮሚቴ እና ስራ አስፈፃሚ በድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ መሰረት እንደሚገመገም አስታውቀዋል። በስብሰባው የፀጥታ ችግሩን በመፍታት ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል የሚያግዝ አቅጣጫ ይጠበቃል ብለዋል ኃላፊው። በዝግ የሚካሄደው ይኸው ስብሰባ ለአራት ተከታታይ ቀናት ይቆያል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም