ኢትዮጵያና እንግሊዝ በንግድና ኢንቨስትመንት መስክ ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ

59
አዲስ አበባ ህዳር 17/2011 ኢትዮጵያና እንግሊዝ በመካከላቸው ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጠናከር ተስማሙ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሂሩት ዘመነ ከእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ሚኒስትር ሃሪያት ባልዲውን ጋር ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል። ሁለቱ ኃላፊዎች ባደረጉት ውይይት በኢትዮጵያና በእንግሊዝ መካከል ያለውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነትን ጨምሮ ሌሎች የትብብር መስኮችን ለማጎልበት ተስማምተዋል። በአፍሪካ ቀንድ ሰላም እና መረጋጋት ብቻ ሳይሆን የምጣኔ ኃብታዊ ትስስሩ የበለጠ እንዲጎለብት እንግሊዝ ድጋፍ እንድምታደርግ ምክትል ሚኒስትሯ ተናግረዋል። በኢትዮጵያና በእንግሊዝ መካከል ከ2 ቢልዮን ዶላር በላይ የሚያወጣ የንግድ ዝውውር እንዳላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም