አልጄሪያ ትርፍ የኤሌክትሪክ ምርቷን ወደ አውሮፓ የመሸጥ ፍላጎት አላት

71
ህዳር 13/2011 አልጄሪያ ከጸሀይ የምታመርተውን ትርፍ የኤሌክትሪክ  ሃይል ወደ አውሮፓ የመሸጥ ፍላጎት እንዳላት የሃገሪቱ የኢነርጂ ሚኒስትር ሙስጠፋ ጉቱኒ  አስታወቁ፡፡ ሚኒስትሩ በመዲናዋ አልጀርስ ይፋ እንዳደረጉት  ሃገሪቱ ወደ አውሮፓ የሃይል ገበያ  ለመቀላቀል ይፋዊ ጥያቄ አቅርባለች ፡፡ ሶስተኛው የአውሮፓ አልጄሪያ  የፖለቲካ ምክክር መድረክ   በሃይል ዙሪያ በአልጀርስ ምክክር የተደረገ ሲሆን ሚኒስትሩና የአውሮፓ የአየር ንብረት ለውጥና የሃይል ኮሚሽነር ሚጉኢል አርያስ ካኒት በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ እንደገለፁት አልጄሪያ ከፀሃይ ሀይል በተጨማሪ ወደ አውሮፓ ህብረት ሃገራት  ጋዝ ለመላክ የሚያስችላትን ውይይት እያደረገች ነው፡፡ ለአብነትም ወደ ስፔን ጋዝ ለመላክ የሚያስችላትን ውል መጠናቀቁ ተገልጿል፡፡ ካንቴ በበኩላቸው አልጄሪያ ለአውሮፓ ዋነኛ የጋዝ አቅርቦት አጋር መሆኗን ገልፀው 13 ከመቶ የህብረቱን ፍላጎት ትሸፍናለች ብለዋል፡፡ አልጄሪያና የአውሮፓ ህብረት በመጪዎቹ አመታትም በሃይል ዙሪያ መስራት የሚያስችላቸውን ስትራተጂክ አጋርነት በአልጀርሱ ጉባኤ እንደመሰረቱ የዘገበው ሲጂቲኤን አፍሪካ ነው፡፡    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም