የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ በርካታ ውጤት የተመዘገበበት ነው

111
አዲስ አበባ ህዳር 9/2011 የአፍሪካ ኅብረት 11ኛው አስቸካይ የመሪዎች ጉባኤ በርካታ ውጤት የተመዘገበት መሆኑን የኅብረቱ ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ ማኅማት ገለጹ። ኮሚሽነሩ ለሁለት ቀናት በአዲስ አበባ የተካሄደውን የህብረቱ አባል አገራት መሪዎች አስቸካይ ጉባኤን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ፤ "ስብሰባው አመርቂ ውጤት የተመዘገበበት ነው" ብለዋል።  በዋነኝነት የኅብረቱን የተኃድሶ እንቅስቃሴ ላይ ትኩረት አድርጎ የተካሄደው ጉባኤው አጠቃላይ የኅብረቱን መዋቅራዊ አሰራር ለማሻሻል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከሩን ጠቅሰዋል። ይህም ኅብረቱ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ግልጸኝነትና ተጠያቂነትን እንዲሁም የተመረጡ ሥራዎች ላይ እንዲያተኩር የሚያደርገው መሆኑን ኮሚሽነሩ አስረድተዋል። ለአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት (ኔፓድ) ሙሉ በሙሉ የኅብረቱ የልማት ኤጀንሲ ሆኖ እንዲቀጥል የተወሰነበትም ስብሰባ አንደሆነ ነው ዶክተር  ማኅማት የተናገሩት። የአፍሪካ የእርስ በእርም መገማገሚያ መደርከም በኅብረቱ ውስጥ እንደ አንድ ተቋም ሆኖ እንደቀጥል መወሰኑ የተቋሙን ተልዕኮ ለማሰካት ወሳኝ መሆኑንም አስረድተዋል። የኅብረቱ አባል አገራት ለኀብረቱ የሚያዋጡትን የ0 ነጥብ 2 በመቶ የቀረጥ ገቢያቸውን እንዲያጠናክሩ ምክክር መደረጉንም ገልጸዋል። ማዕቀብ የተጣለባቸውም በተመሳሳይ የሚጠበቀብቻውን ገቢ ለማዋጣት ሰፊ ምክክር ተካሂዷል ነው ያሉት። በአጠቃላይ በዚህ ሰብሰባ በርካታ ውጤቶች ቢመዘገቡም አሁንም በርካታ ሥራዎች እንደሚቀሩ ነው የህብረቱ ኮሚሽን ኮሚሽነር ያስታወቁት። እስካሁን የተከናወኑት ተግባራት አህጉሪቷ ከምትፈልገው አንጻር ትንሽ መሆኑን ገልጸው የተጀመረው ተኃድሶ መሰረቱን ጥሎታል ነው ያሉት። የወቅቱ የኅብረቱ ሊቀ-መንበርም ስብሰባው ውጤታማ መሆኑን ገልጸው አሁንም የተኃድሶ እንቅስቃሴውን ከግብ ለማድረስ መሰራት አለበት ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም