ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሲሼልስ ፕሬዚዳንት ዳኒ ፋውሬ ጋር ተወያዩ

61
አዲስ አበባ  ህዳር 7/2011 ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ከሲሼልሱ አቻቸው ዳኒ ፋውሬ ጋር የሁለቱን አገራት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዩች ላይ ተወያይተዋል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ለ11ኛው የአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ስብሰባ አዲስ አበባ የሚገኙትን የሲሼልሱን ፕሬዚዳንት ዳኒ ፋውሬ ዛሬ  በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ሁለቱ መሪዎች የሁለቱን አገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል። የሲሼልሱ ፕሬዚዳንት ዳኒ ፋውሬ ከውይይቱ በኋላ ለጋዜጠኞቸ በሰጡት ቃል ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ  የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሄር ሆነው በመመረጣቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልፀዋል። ፕሬዚዳንቷ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎቸ የቆዩ በመሆናቸው ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአህጉሪቷም የሚኖራቸው አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑን ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያና ሲሼልስ እንደ አውሮጳውያን አቆጣጠር ከ1982 አንስቶ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጀምረዋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም