አቶ ያሬድ ዘሪሁን ነገ ከሰዓት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

508

አዲስ አበባ ህዳር 6/2011 የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የቀድሞው ምክትል ኃላፊ እና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን ነገ ህዳር 7 ቀን 2011 ዓ.ም ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ተወስኗል።

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩት አቶ ያሬድ በቁጥጥር ስር የዋሉት በትናንትናው ዕለት በዱከም ከተማ በፌዴራል ፖሊስና በኦሮሚያ ፖሊስ ክትትል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተመሳሳይ የኢትዮ-ቴሌኮም የሴኪዩሪቲ ዲቪዥን ኃላፊ ኮሎኔል ጉደታ ኦላና በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ኃላፊው በሜቴክ የተፈፀመውን የሙስና ወንጀል የሚያጣሩ ባለሙያዎች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ በማድረስና የአቃቤ ህግ ስራን በማወክና በማሰናከል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ነው ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የገለጸው።