ሁመራ ላይ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉት ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው ተይዘው አዲስ አበባ ገቡ

118
አዲስ አበባ ህዳር 4/2011 ሁመራ ላይ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉት የቀድሞው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ዋና ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው በፖሊስ ተይዘው አዲስ አበባ ገቡ። ብርጋዴር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽንን ሀብት በመመዝበር ተጠርጥረው የእስር ትዕዛዝ ወጥቶባቸው ቆይተዋል። በዚህም በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል ወደ ሱዳን ሊኮበልሉ ሲሉ ሁመራ አካባቢ በጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የፌዴራል አቃቤ ሕግ ኮርፖሬሽኑ ከ2004-2010 ዓ.ም ድረስ ከ37 ቢሊዮን ብር በላይ የውጭ አገር ግዥ ያለጨረታ መፈጸሙን ትናንት መግለጹ ይታወቃል። ኮርፖሬሽኑ የመንግሥት አስራርና ሕግ በመተላለፍ ትላልቅ የአገር ውስጥና የውጭ አገር ግዥዎችን ሲፈጽም ቆይቷል። ከተጠርጣሪዎች መካከል ከአራት ግለሰቦች በስተቀር ቀሪዎቹ በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን በተለያዩ የስራ ሃላፊነቶች ላይ ያገለገሉ ናቸው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም