ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን አዲስ የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ይፋ ሆነ

75
አዲስ አበባ ህዳር 4/2011 አሁን በስራ ላይ ያለውን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመከለስ አዲስ ዋጋ ማዘጋጀቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ። ከ ህዳር 4 እስከ 30 - 2011 ዓ.ም ተግባራዊ የሚሆነው የዋጋ ክለሳ የዓለም የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ጭማሪ እያሳየ መምጣቱን ተከትሎ መዘጋጀቱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በዚሁ መሰረት ቤንዚን በሊትር 19 ብር ከ69 ሣንቲም፣ ነጭ ናፍጣ 17 ብር ከ78፣ ኬሮሲን 17 ብር ከ78፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ 15 ብር ከ41፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ 14 ብር ከ90፣ የአውሮፕላን ነዳጅ 27 ብር ከ08 ሣንቲም በሊትር እንዲሆን ተወስኗል። ሚኒስቴሩ የዋጋ ማስተካከያውን አስመልክቶ ባዘጋጀው የህዝብ ማስታወቂያ የተካተቱ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ዝርዝር በነገው የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ እንደሚወጣና በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች በሚገኙ ሁሉም ማደያዎች ተግባራዊ እንደሚሆን አስታውቋል።    
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም